Our Products

የምርምር ውጤቶቹ እና ዋና ዋና ጠቀሜታቸው ማጠቃለያ

1. መካኒካል የሆነ የውሀ ማምረቻና ማጠራቀሚያ ማሣሪያ (Water harvesting and reserving device called TGLS)

 • የእያንዳንዱን ገበሬ ደረቅ ማሳዎች ሁሉ በበጋ ወደ መስኖ ማሳነት በመቀየር የገበሬው መሬት ክረምት ሳይጠብቅ ዓመታቶችን ሁሉ የማይቋረጥ ከፍተኛ ምርት እንዲሰጥ ያደርጋል፡፡ መሳሪያውን በመጠቀም በትንሽ መሬት ላይ የማያቋርጥ ምርት በማምረት የመሬት ጥበትን ያስወግዳል፡፡
 • መሳሪያው በማንኛውም ቦታ አየር ያለምንም ሞተር ኤሌክትሪክ፣ ነዳጅ ፍጆታ በራሱ ስልት ብቻ ተግባሩን የሚያከናውን በመሆኑ ገበሬውን ከማናቸውም ወጪና የቴክኒክ ችግር ይጠብቃል፡፡
 • የውሀ ጎተራን በማከማቸት ለማሳው፣ ለሚጠጣውና ለከብቱም በቂ ንጹህ ውሀ ከቤቱ እንዲያገኝ በማድረግ ከፍተኛ አገልግሎትን ይሰጣል፡፡ ይህ መሣሪያ የሰው ልጆችን የምግብና የንጹህ መጠጥ ውሀ ዋስትናን ለዘለቄታው በማይቋረጥ ሁኔታ ያረጋግጣል፡፡
 • ገበሬው በዚህ መሣሪያ በመጠቀሙ ሴቶችን እና ሕጻናትን ከውሀ ሸክም ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚገላግል መሳሪያ ነው፡፡
 • ገበሬው በዚህ መሣሪያ በመጠቀም የኮንስትራክሽን እና ለሌሎች ግልጋሎቶች የሚውል የተትረፈረፈ የደን ልማትን ለማከናወን ይችላል፡፡ የአካባቢ አየር፣ አፈር እና የብዝሀ ሕይወት ጥበቃን እና ዋስትናን ያረጋግጣል፡፡
 • በአጠቃላይም ይህ መሳሪያ ሀገራችንን ብሎም ዓለምን በዚህ መሳሪያ ወደ አረንጓዴ ገነትነት ለመቀየር የሚያስችል መሣሪያ ለመፍጠር ነው፡፡
 • 2. በተፈጥሮ ጊዜያዊ የሆኑ ሰብሎችን አንዴ ብቻ ተዘርተው ቋሚ ሰብል እንዲሰጡ የሚያስችሉ ዘሮችን ማባዛት (Perennial automatic crops)

 • የማይሞቱ ሰብሎችን በማምረት ከፍተኛ ምርት ለማግኘት ያስችላል፡፡
 • በዓመት አንዴ ብቻ የተለያየ ዝርያ ያላቸውን ሰብሎች በዓመት ከሁለት እስከ አራት ጊዜ ያለማቋረጥ ለማምረት ያስችላል፡፡
 • 3. በተፈጥሮ የተዘጋጀ ማዳበሪያና የአፈር መድሀኒት ማቀነባበር (Agro fuel fertilizer)

 • ለቅስመ አፈር ህክምናና ጥገና የሚያገለግሉ ንጥረ ነገሮችን የያዘ መሆኑ
 • ለማናቸውም ሰብሎችና የአፈር አይነት እጅግ ጠቃሚ የሆነ መሆኑ
 • ጉዳት አልባ የሆነና የ ፒ. ኤች. 7 ይዘት ያለው (real pH = 7.09) ያለው መሆኑ
 • የህይወት ማበልፀጊያ ግሪን ሌቭላይዘር (Green Levilizer) ደረጃ ያለው መሆኑ
 • ማይክሮ እና ማክሮ ንጥረ ነገሮችን (Nutrients) የያዘ መሆኑ
 • ለሁሉም ሰብሎች ሁለንተናዊ እድገት አስፈላጊ የሆኑ ንጥረ ነገሮችን በዋናነት (NPK) የያዘ መሆኑ
 • ከአርተፊሻል ኬሚካል በፀዳ ሁኔታ ኦርጋኒክ ንጥረ ነገሮችን (package of nutrients) የያዘ መሆኑ፤
 • የተፈጥሮ ተግባራቶችን ለማከናወን የሚያግዙ በርካታ ንጥረ ነገሮችን የያዘ መሆኑ፤
 • CEC-14 real pH=7.09 neutral levelizer ደረጃ ያለው መሆኑ
 • በግብርና ምርምር ላቦራቶሪ ተረጋግጦ ሰርተፊኬት ያለው መሆኑ
 • ከጥቅሞቹ በጥቂቱ

 • በውስጡ አፈርን የሚጎዱ ኬሚካሎችን የሚቆጣጠርና የሚያጠፋ የጎደለውንም ሬዚስታንስ የሚሞሉ፤
 • በዝናብ ውሀ አማካይነት ከወንዝ ውሀ ጋር ቢቀላቀልም በብዝሀ ህይወት ላይ ጉዳት የማያመጣ፣
 • ማናቸውንም አይነት በአፈርና በውሀ ውስጥ ያሉ ጎጂ (በእፅዋትና፤ በሰው እንዲሁም በብዝሀ ህይወት አጠቃላይ ጤንነት ላይ) ጉዳት ፈጣሪ ኬሚካሎችን ኒውትራላይዝ የማድረግ ብቃት ያለው መሆኑ፣
 • በውስጡ አፈርን የሚያለሰልሱ እና የሚያብላሉ ባክቴሪያዎች ላይ ጉዳት የሚያደርሱ ኬሚካሎችን ያስቀራል
 • በቀላሉ ጠቃሚ ንጥረ ነገሮችን ለእፅዋት የመልቀቅ ሀይሉ በሶስት እጅ ከፍ ያለ መሆኑ፣
 • በውስጡ አየር፤ውሀ እና ንጥረ ነገሮች እንደልባቸው እንዲዘዋወሩ የሚያደርግ መሆኑ፣