Message from the Researcher Amharic
የተመራማሪው መልዕክት

የሳይንሱ ዓላማ በሰው ልጆች እና በተፈጥሮ ምርጫ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መካከል ያለውን መሰረታዊ ቅራኔ መፍታትና የሰው ልጆች ሳይንስና ቴክኖሎጂ የተፈጥሮ ምርጫ ሳይንስን እንዲታጠቅ በማድረግ በምድር ሰላማዊ የሳይንስ ሽግግር እንዲፈጠር ማድረግ ነው፡፡

ምርምር ለማድረግ ያነሳሳኝ ፍልስፍና እና ራዕይ በአጭሩ አሁን ባለው የሰው ልጆች ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና በተፈጥሮ ሳይንስና ቴክኖሎጂ መካከል ፈፅሞ የማይታረቅ ልዩነት በመኖሩ የሰው ልጅ ሳይንስ ከተፈጥሮ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ላይ ያልተመሰረተ ሳይንስ ባለቤት በመሆኑ የሰው ልጅ በአሁኑ ሳይንስ የቱንም ያህል ቢማርና ቢሰለጥንም ለተፈጥሮ ሳይንስ የተማረ እንግዳ ሆኖ የሚኖር የምንከተለው ሳይንስና ቴክኖሎጂም የተፈጥሮ ነገሮችን ሁሉ በተፈጥሮ ፎርሙላቸው መልሶ ማከምና መጠገን የማይችል በመሆኑ እና በማናቸውም የተፈጥሮ ነገሮች ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል እንዲሁም የሰው ልጆችን የተፈጥሮ ምርጫ ሳይንስ እውቀትና ባለቤት እንዳይሆኑ የሚገድብ ከመሆኑም በላይ የምንከተለው ሳይንስና ቴክኖሎጂ መሰረታዊ አላማ በሁሉም የሳይንስ ዘርፍ የቲዎሪና ፕሪንሲፕል (theory and concept) ላይ ያተኮረ በመሆኑ ይህ ደግሞ የተፈጥሮ ሳይንስ መግቢያ ሀ፣ሁ(ABCD)መሆኑ ነው፡፡

የሰው ልጅ ሳይንስ መሰረታዊ አላማ የተፈጥሮ ንጥረ ቁሶችን ወደ አርቲፊሻል ሳይንስና ቴክኖሎጂ በመቀየር ለዘመናት ጥረት ያገኘው ግንዛቤና ፎርሙላ እንዲሆኑ በማድረግ የተፈጥሮ ምርጫ ሳይንስና ቴክኖሎጂን ሙሉ በሙሉ የሚያቋርጥ አደገኛ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ባለቤት ከማድረግ አልፎ በተፈጥሮ ላይ የምናደርሰውን ማናቸውንም ጉዳት ለመረዳትና ለማወቅ እንዲሁም ያደረስነውን ጉዳትና ጥፋትን ለመመዘን፣ለመለካት፣መልሶ ለማከምና ለመጠገን እና ለማሻሻል የማያስችለን ሳይንስና ቴክኖሎጂ መሆኑ ነው፡፡

በተጨማሪ ማናቸውንም የተፈጥሮ ችግሮችን ሁሉ በአርቴፊሻል ሳይንስና ቴክኖሎጂ ስልትና ቴክኒክ ለማስተካከል የምንሞክር በመሆናችን ይህ ደግሞ ለተፈጥሮ ችግር የተፈጥሮ መፍትሄ ከመስጠት ይልቅ አርቴፊሻል መፍትሄ በመስጠት የባሰ ለተፈጥሮና ለራሱም ለሰው ልጆችም በህይወት በምድር ላይ የመኖር ዋስትናችንን ከማረጋገጥ ይልቅ ህልፈታችንን የሚያፋጥን አደገኛ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ውስጥ ራሳችንን ለማጥፋት ታጥቀን እንገኛለን፡፡

ይህ ሳይንስ የሰው ልጆችን ሕይወት ከተፈጥሮ ሲስተም ውጪ በሆነ አርቲፊሻል ሳይንስ በተገኙ ውጤቶች ከተፈጥሮአዊ ሕይወት ሂደት ውጪ በከፍተኛ ደረጃ የለወጠ ቢሆንም ነገር ግን ከተፈጥሮ ግንባታ ሂደት ደግሞ እጅግ ተቃራኒ የሆነ ሳይንስ የምንጠቀም በመሆናችን መራዥ ኢንዱስትሪዎችን የምንጠቀም በመሆኑ በተፈጥሮ ምርጫ ሳይንስ እና በሰው ልጅ ሕይወትና ህልውና ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል እና በምድር፣በከባቢ አየር ፀባይ፣ በአፈር፣ በውሀ፣ወ.ዘ.ተ. ላይ ጉዳት በማስከተል የህልውናችንን መሠረት በማናጋትና በማፍረስ ላይ ይገኛል፡፡

ይህ ሳይንስ ደግሞ የሳይንስ መጀመሪያው ቲዎሪ ምዕራፍ አንድ ሲሆን ይህን የሰው ሰራሽ ሳይንስን ሂደት ካልተቀለበሰ ወይም ካልተቀየረ በስተቀር የሚያስከትለው አደጋ በዚህም የማይቆምና ለቀጣዮ ትውልድ የሚተላለፍ እንዲሁም በሰዎችና በሌሎች ፍጥረታት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ በመሆኑ ይህ ሂደት ለረጅም ዘመናት ሲያስጨንቀኝ የኖረ በመሆኑ ይህንን የሳይንስ ምዕራፍ ለመተካት የሚያስቸለውን የተፈጥሮ ምርጫ ሳይንስና ተፈጥሮ አገዝ ሲስተም የሚከተል አዲስ የተፈጥሮ ምርጫ ኢተርናል ላይፍ ባዮሎጂ ሳይንስን ለመተግበር የሚያስችለንን ምዕራፍ ሁለትን መክፈት እንዲቻል 1969 ዓ.ም. ጀምሮ ለ5 ዓመታት የችግሩን ቅድመ ጥናት እና የመፍትሔ ሀሳብ ፍለጋ እንዲሁም ከ35 ዓመታት በላይ ደግሞ የተግባር ጥናትና ምርምር በማድረግ እና ቲዎሪውን በመቀመር በድምሩ ከ40 ዓመታት በላይ ተመራምሬ ለሕልውናችን ጠቃሚና ችግር ፈቺ ምርቶችን ለማምረት ችያለሁ፡፡

የድርጅቱ ዝርዝር ሁኔታ

የድርጅቱ ስም

ሬኔቸር ኢተርናል ላይፍ አግሮ ፕሮሰሲንግ አ.ማ.

2. የድርጅቱ አደረጃጀት

የድርጅቱ በሰነዶች ማረጋገጫ ጽ/ቤት የተረጋገጠ በ10 መስራች አባላት የፀደቀ የመመስረቻና የመተዳደሪያ ደንብ ያለው ሲሆን ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድ ሚኒስቴር የዋና የንግድ ምዝገባ ሠርተፊኬት፣ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ገቢዎችና ጉምሩክ ባለስልጣን የቲን ሠርተፊኬት እና ከአዲስ አበባ ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ የኢንቨስትመንት ፍቃድ አውጥቶ ገንዘብ በመመደብ ከሌሎች የንግድ ሸሪኮች ጋር በመሆን የኦርጋኒክ ማዳበሪያ ለማምረት በእንቅስቃሴ ላይ ይገኛል፡፡

3. የድርጅቱ ምርቶች

የድርጅቱ በመጀመሪያ ስትራቴጂክ ዓላማው አካቶ የሚያመርታቸው ሶስት ዋና ዋና የግብርና ግብአቶች ማለትም አንዴ ብቻ ተዘርተው ቋሚ ሰብል እንዲሰጡ የሚያስችሉ ዘሮችን ማባዛት፣ ከዝናብ ውሀ የሚሰበስብና የሚያጠራቅም መሳሪያ እና ከተፈጥሮ ግብአት የተዘጋጀ ኦርጋኒክ ማዳበሪያ ናቸው፡፡ እነዚህ ምርቶች ከሚመለከታቸው የመንግስት አካላት የባለቤትነት ሰርተፊኬትና የናሙና የላቦራቶሪ ፍተሻ የተሰጣቸው ናቸው፡፡

4. የድርጅቱ አድራሻ

- ሀገር፡ ኢትዮጵያ
- ከተማ፡ አዲስ አበባ
- ክፍለ ከተማ፡ ቦሌ
- ወረዳ/ቀበሌ፡ 02
- የቤት ቁጥር፡ አዲስ፣ ኤደን ህንጻ፣4ኛ ፎቅ፣ የቢሮ ቁጥር 07

5. የንግዱ ዓይነት

ሁሉን አቀፍ የግብርና እና የኢንዱስትሪ ክላስተር ማለትም ሪስፔሻላይዝድ ሜካናዛይሼሽን ተግባር ሆኖ የንግድ ዕቃዎችን የማምረት ሥራን፣ የግብርና ልማትን ለማሳለጥ የሚያገለግሉ ግብአቶችን ማምረት እና የምርምርና ስርፀት ስራዎችን መስራት ያጠቃልላል፡፡

6. የማምረት ደረጃ

ካምፓኒው የሚሰራው ስራ በአነስተኛ ኢንዱስትሪ ደረጃ ቢሆንም ወደ ከፍተኛ ደረጃ የማሳደግና አለም አቀፋዊ የንግድ ተቋም ለመሆን ይሠራል፡፡

ምስሎች

  • ሁሉም ምስሎች
  • የምስክር ወረቀት

Vidios